ኢትዮጵያ ከ70 አመታት በፊት ለእንግሊዝ በእርዳታ ቡና መላኳን ያውቃሉ?
እ.ኤ.አ በ1953…
የካቲት 1 ቀን ንጋት ላይ…
የእንግሊዝና የስኮትላንድ ምሥራቃዊ የባህር ዳርቻ አካባቢዎች በአስከፊ የጎርፍ አደጋ ተመቱ፡፡ በእንግሊዝ 307፣ በስኮትላንድ ደግሞ 19 ሰዎችን ለህልፈተ ህይወት የዳረገው አስከፊ የጎርፍ አደጋ፣ ሃያ አራት ሺህ ቤቶችን ክፉኛ ሲያፈራርስ፣ ሰላሳ ሺህ ሰዎችን ከመኖሪያቸው አፈናቀለ፡፡
ስለ አደጋውም ሆነ የአገራቱ መንግሥታት በጎርፉ አደጋ የተጎዱትንና የተፈናቀሉትን ወገኖች ለማቋቋም ስላደረጉት ጥረት መገናኛ ብዙሃን ብዙ ቢሉም፣ ኢትዮጵያ በወቅቱ ለእንግሊዝ መንግሥት በእርዳታ መልክ ስለላከችው ታላቅ ስጦታ በጥቂቱም ቢሆን መወራት የተጀመረው ግን አደጋው ከተከሰተ ከ60 ዓመታት በኋላ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2012፣ ጥር 18 ቀን፤ ጎልዲንግ ያንግ የተባለው የእንግሊዝ አጫራች ኩባንያ፣ በሊንከን የሽያጭ ማዕከሉ ለእለቱ ቀጠሮ የያዘለትን ጨረታ ደወል አስደውሎ በይፋ አስከፈተ፡፡ ኩባንያው በዕለቱ ለጨረታ ካቀረባቸው ነገሮች መካከል፣ በጨረታ መለያ ቁጥር 345 ለሽያጭ የቀረበው ለዘመናት ታሽጎ የኖረ አንድ ታሪካዊ ጣሳ ይገኝበታል፡፡
“እ.ኤ.አ በ1953 በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የተጎዱትን ለማቋቋም፣ ከግርማዊ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገስት፣ ለግርማዊት ንግሥት በስጦታ መልክ የተበረከተ፣ እሽግ የቡና ጣሳ” የሚል አጭር የጽሁፍ መግለጫ ሰፍሮበታል ጣሳው፡፡
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በወቅቱ ወደ እንግሊዝ የላኩት ይህ መጠነኛ የቡና ጣሳ፣ በዕለቱ በተከናወነው ጨረታ፣ በ22 የእንግሊዝ ፓውንድ መሸጡን በአንግሎ ኢትዮጵያን ሶሳይቲ ድረ-ገጽ ለንባብ የበቃ አንድ ጽሁፍ ያስታውሳል፡፡
አና ፓርሰንስ የተባለች እንግሊዛዊት የጻፈችው ይህ ማስታወሻ፣ ማርክ ሰርጃንት የተባለ አንድ እንግሊዛዊ እ.ኤ.አ በ2007 ታይም ኤንድ ታይድ በተባለው ሙዚየም በተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ላይ በጨረታ ከተሸጠው ጣሳ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሌላ የኢትዮጵያ ቡና ጣሳ ለእይታ ቀርቦ ማየቱንም ይጠቅሳል፡፡
ቢቢሲ በበኩሉ፤ እ.ኤ.አ በ2013 ጥር ወር ላይ ሜልቪን ኢን ዘ ሞርኒንግ በተባለው የሬዲዮ ፕሮግራሙ፣ የጎርፍ አደጋውን 60ኛ አመት ማስታወሻ በተመለከተ በሰራው ዘገባ፣ ኢትዮጵያ ለእንግሊዝ የአደጋው ተጎጂዎች ማቋቋሚያ የላከችውን ቡና ጉዳይ በአጭሩ ጠቅሶታል፡፡
በአንግሎ ኢትዮጵያን ሶሳይቲ ድረ-ገጽ ስለጉዳዩ የጻፈችው አና ፓርሰንስ፣ ኢትዮጵያ ለእንግሊዝ የላከችውን የቡና እርዳታ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ባደረገችው ጥረት፣ ሱዛን ኒኮላስ የተባለች አንዲት እንግሊዛዊት፣ እ.ኤ.አ በ2013 በአባቷ ጋራዥ ውስጥ ስላገኘችው ተመሳሳይ በርሜል መስማቷንም ትጠቅሳለች፡፡
የዚህ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ከላይ የጠቀስናቸውን መረጃዎች ይዞ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ፍንጮችን ለማግኘት ባደረገው ጥረት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ከጥቂት ጊዜያት በፊት፣ በሊንክዲን ድረገጹ ይፋ ያደረገውን አስገራሚ መረጃ ሊያገኝ ችሏል፡፡ ጥንታዊ ደብዳቤ፣ ኢትዮጵያ በ1947 ዓ.ም የጎርፍ አደጋ ደርሶባት ለነበረችው ሆላንድ (ኔዘርላድ)፣ 25 ቶን ከ500 ኪሎ ግራም የሚመዝን ቡና በእርዳታ መልክ መላኳን ያረጋግጣል፡፡
ሚያዝያ 26ቀን 1947 ዓ.ም፤ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ለጠቅላይ ግምጃ ቤት የጻፈው ይህ ደብዳቤ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ ለሆላንድ በእርዳታ መልክ የላከው ቡና፣ ከእነ መላኪያውና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ጋር፣ በወቅቱ የገበያ ዋጋ፣ 67,656.30 ብር (ስድሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከ30 ሳንቲም) እንደሚገመትም ያመለክታል፡፡
በዚህ ደብዳቤ የተገለጸው የቡና እርዳታ ወደ ሆላንድ የተላከበት ጊዜ፣ ቀደም ብለው የተጠቀሱት የቡና እርዳታዎች ወደ እንግሊዝ ከተላኩበት ጊዜ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፣ እንዲሁም የተለያዩ የመረጃ ምንጮች በዚያ ጊዜ በእንግሊዝም በሆላንድም ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋዎች ተከስተው እንደነበር ማረጋገጣቸውን በማጤን፤ በሁለቱ የቡና ስጦታዎች መካከል ግንኙነት ሊኖር እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡
(የኢትዮጵያ ቡና ማህበር 50ኛ ዓመት ልዩ መጽሔት፤ የካቲት 2015)
* ኢትዮጵያ ለሆላንድ ከ25 ቶን በላይ ቡና በእርዳታ መላኳንም አንድ ጥንታዊ ደብዳቤ አረጋግጧል
የአበበ ገላው ነገር
ክፍል ፪
አበበ ገላው ከቀናት በፊት “የአበበ ገላው ነገር. . .” በሚል ለጻፍኹበት ትችት ዛሬ “ይድረስ ለአቶ አቻምየለህ ታምሩ” በሚል ርዕስ በሰጠው “ግብረ መልስ” ለቀረበበት ለአንዱም ትችት መልስ ሳይሰጥ “ተሳዳቢ፣ ተራጋሚ፣ ቅንነት የጎደለው”፣ ወዘተረፈ በማለት የቀረበበትን ትችት ለመከላከል ሳይሞክር “ስድብ አላዥጎደጉድም” ፤ የመሳደብ መብትህን አልጋፋም” በማለት ሰው ይታዘበኛ እንኳን ሳይል “ተሳዳቢ፣ ተራጋሚ፣ ቅንነት የጎደለው” የሚሉ ስድቦችን እያዥጎደጎደ ራሱን እንዳልተሳደበ አድርጎ በማቅረብ አጀንዳ ለማስቀየር ሞክሯል።
አበበ አጀንዳ ለማስቀየር 6 ነገሮችን ዘርዝሯል። ከዘረዘራቸው ከስድስቱ ነገሮች ውስጥ ከቀረበበት ትችት ጋር የሚገናኙ ሁለቱ ብቻ ናቸው። የተቀሩት ራሱን አንቱ እያለ ስለራሱ ያቀረባቸው መወድሶች ስለኾኑ አስተያየት ልሰጥባቸው አልሻም። ካቀረብኹበት ትችት ጋር በተያያዘ ስላነሳቸው ሁለት ጉዳዮች ግን አስተያየት መስጠት እሻለኹ።
አበበ ዐቢይ አሕመድ የሪፑብሊካን ጠባቂ አልመደበልኝም ብሎ ክዷል። አበበ ሪፑብሊካን ጋር ጠባቂ አልተመደበልኝም ብሎ የካደው ማስረጃ የሌለ መስሎት ነው። የዐቢይ አሕመድ የሪፐብሊካን ጠባቂ አራት ዋና ዋና መዋቅሮች አሉት፤ አንደኛው የሲቪል ልብስ የሚለብሱ ቪአይፒ ጥበቃን ወይም በማንኛውም ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትር ተብዮው እና ከርሱ ጋር የሚቀራረቡን የሚጠብቁ ናቸው። ሁለተኛው የሪፑብሊካን ጋርድ መዋቅር ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዮው የሚከተሉ ባለ ቀይ ቦኔት ወታደሮችን ነው። የተቀሩትን ሁለት መዋቅሮች በመዘርዘር የአንባቢን ጊዜ መሻማት ስለማያስፈልግ የሪፐብሊካን ጠባቂ ተብዮውን አራት ዋና ዋና መዋቅሮች ማወቅ የሚሻ ቢኖር ጠባቂው የተቋቋመበትን መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 426-2018 ይመለከት ዘንድ በመጋበዝ ወደ ነጥቤ ልሻገር።
አበበ ገላው አዲስ አበባ ሲመላለስ ሲጠበቅ የነበረው የሲቪል ልብስ በሚለብሱ፣ ቪ.አይ.ፒ ጥበቃን ወይም በማንኛውም ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትር ተብዮው እና ከርሱ ጋር የሚቀራረቡን በሚጠብቁት የሪፑብሊካን ጠባቂዎች ነው። ባጭሩ አበበ ገላው በዐቢይ አሕመድ ቅልቦች ወይም ሪፑብሊካን ጋርድ አባላት ይጠበቅ ነበር። ይህም ከታች በታተመው የፎቶ ማስረጃ ላይ ይታያል።
ሌላው አበበ የአማራ ታጋዮችን በጽንፈኛነት አልከሰስኹም፤ የኢሜሌን ይዘት ሙሉ በሙሉ አልተረዳኸውም ሲል ለመተቸት ሞክሯል። ይገርማል! አበበ እ.ኤ.አ. ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ ታጋዮችን በጽንፈኛነት፣ በተሳደቢነት፣ ወዘተ ሲከስና ሲያወግዝ የኖረውን ትተን ለዐቢይ አሕመድ የጻፈው አምልኮተ ዐቢይ [አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ ለሚባለው ኮልኮሌ በኢሜል በጻፈው ማመልከቻ with your caliber and vision እያለ የቆለለውን ልብ ይሏል] ብቻ ወስደን እንኳን ብናይ የአማራ ታጋዮች በጽንፈኛነት የከሰሰበትን እናገኛለን።
አበበ በጻፈው አምልኮተ ዐቢይ ላይ እንደጠቀሰው አረመኔው ዐቢይ አሕመድ የአማራ አንቂዎችን ጠርቶ ለማነጋገር የተገደደው አማራ ክልል በሚባለው ክልል ውስጥ ጽንፈኛነት እያደገ በመምጣቱ እንደኾነ ነግሮኛል ብሎናል። አበበ ገላው ለዚህ የዐቢይ አሕመድ ክስ የሰጠው መልስ “አማራን አትግደሉ”፤ “አማራን አታፈናቅሉ”፤ “አማራ እንዳይወለድ የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡርን ሆድ ቀድደው ጽንስ የሚያወጡትን”፣ ወዘተ የሚቃወሙ የግፉአን ድምጾች እንጂ የአማራ ጽንፈኛ በአማራ ሕዝብ መካከል የለም የሚል መልስ አይደለም።
አረመኔው ዐቢይ አሕመድ የአማራ ጽንፈኛ አስቸገረኝ ሲል ለነገረው የግፍ ክስ የአበበ ገላው መልስ “እውነት ነው በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል [የአማራ ክልል የሚባለውን ጨምሮ] የሚታየው ጽንፈኛነት ከፍተኛ አደጋ ነው” የሚል ነው። በአማራ ክልል ተብዮው ጭምር የሚታየው ጽንፈኛነት ከፍተኛ አደጋ ነው ሲል ከዐቢይ አሕመድ የግፍ ክስ ጋር የተስማማው አበበ ገላው ነው እንግዲህ የአማራ ታጋዮችን በጽንፈኛነት አልከሰስኹም እያለ አይናችኹን ጨፍኑና ላሞኛችኹ የሚለን።
ባጭሩ አበበ ገላው አረመኔው ዐቢይ አሕመድን ሲያመልክ በባጀባቸው ያለፉት አምስት አመታት ውስጥ ለቀረበበት ትችት የሰጠው አንድም መልስ ወይም ማስተባበያ የለም። ለማስታወስ ያህል ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ አበበ ገላው እንዲህ እያለ ዐቢይ አሕመድን ሲያመልክ ኖሯል፤
1. አዲስ አበባን የኦሮሞ ናት ያለው ዐቢይ አሕመድ የሚመራው ኦዴፓ ሳይኾን የኦሮምያ ክልል ነው፤
2. በዐቢይ አሕመድ ላይ እኔ ጥያቄ የለኝም፤ ሌሎችም ሊኖራቸው አይገባም፤
3. ዐቢይን የመሰለ ብቃት ያለው መሪ ኢትዮጵያ ኖሯት አያውቅም፤
4. ዐቢይ አሕመድ በወያኔ ዘመን ስልክ መጥለፍ የለብንም ብሎ ስለ እኛ ከነ መለስ ጋር ተጣልቶ ከኢንሳ ተባሮልናል፤
5. የአንድ ክፍለ ከተማ ሕዝብ አፈናቅሎ በ49 ቢሊዮን ብር በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት ቅንጡ ቤተ መንግሥት እየገነባ ያለን አረመኔ ዐቢይ አሕመድ ቤተ መንግሥት ሳይኾን ትናንት ቢሮዎች ነው የሚያስፈልጉን ብሎ የሚያስብ የሕዝብና የሕዝብ ጉዳት የሚጋራ መሪ ነው፤
6. የዐቢይ አሕመድን የውሸት የትምህርት ማስረጃ ለመሸፈን ደግሞ “የሚስጥሩ ቁልፍ” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ውዳሴ ዐቢይ ዶክመንተሪ ሰርቷል፤
እኒህንና መሰል አምልኮተ ዐቢይ አሕመድ ዝባዝንኬዎችን ሲደረድር የኖረው አበበ ገላው ንስሀ ገብቶና ያሳሳተቸውን ሰዎች ይቅርታ ጠይቆ ራሱን ለሕዝብ ፍርድ ማቅረብ አለበት።
አበበ ገላው ለእነዚህና መሰል ለቀረቡበት ትችቶች መልስ ሳይሰጥ፣ ሲደረድረው ስለኖረው አምልኮተ ዐቢይ አሕመድ ይቅርታ ሳይጠይቅና ራሱን ለሕዝብ ፍርድ ሳያቀርብ ዛሬ ላይ ዐቢይ አሕመድ የሚባለው አውሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰው ስላለው አረመኔነት ከደሙ ንጹህ ነኝ ብሎ እጆቹን ታጠበ ሊቀመጥ አይችልም።
አረመኔው ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በደረሰበት እንዲደርስ “በዐቢይ አሕመድ ላይ እኔ ጥያቄ የለኝም፤ ሌሎችም ሊኖራቸው አይገባም” እያሉና የውሸት ትምህርቱን የእውነት ለማስመሰል የውሸት ዶክመንተሪ እየሰሩ ስር እንዲተክል ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩት እነ አበበ ገላውና መሰል አምላኪዎች አስተዋጽኦ አድርገዋል። ስለኾነም ተጠያዊ ናቸው።
እሬቻ ከገዳ የወረራ ሥርዓት ጋር ምን ያገናኘዋል? እሬቻስ የማን በዓል/ባሕል ነው?
ኢትዮጵያ ውስጥ የተዘረጋው አረመኔያዊ የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ የኾነው ዐቢይ አሕመድ ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ እሬቻን የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል ነው ብሎናል። እሱና በስሩ የኮለኮላቸው የአፓርታይድ አገዛዙ ፊታውራሪዎች ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ጥንታዊቱን በራራን፤ ዘመናዊቱን አዲስ አበባን አፍርሰው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ ውስጥ በተፈጠረችው ፊንፊኔ ለመተካት ያላፈረሱት የቆየ አሻራና የከተማይቱን ጥንታዊነት የሚመሰክር ምልክት የለም።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የፖሊስ ሠራዊት ኦሮሚያ ከሚባለው ክልል በመለመሏቸው ለከተማው ከባሕር የወጣ አሳ በሆኑ የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ቄሮዎች ተክተውታል። ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ ከመስቀል በኋላ ይከበር የነበረውን እሬቻን “ሸገርን ለማስዋብ” በሚል ዐቢይ አሕመድ ግለሰቦችን [አብዛኛዎቹ አማሮች ናቸው] አምስት ሚሊዮን ብር እንዲያወጡ አድርጎ ያስቋረውን ሰው ሰራሽ ሐይቅ “ሆራ ፊንፊኔ” የሚል ስያሜ በማውጣት እሬቻን አዲስ አበባ ውስጥ እንዲከበር አድርገዋል።
ሽመለስ አብዲሳ በሸራተን አዲስ እሬቻን አስመልክቶ በኦሮሚፋ ባደረገው ዲስኩር “እሬቻ ወደ አዲስ አበባ ወደ ጥንቱ እሴት ተመልሶ እንዲከበር ውሳኔ የተላለፈው በጠቅላይ ሚኒስትራችን በዶክተር ዐቢይ አሕመድ ነው” ሲል ነግሮናል። ይህን የሽመልስ አብዲሳ ምስክርነት ይዘን የዐቢይ አሕመድን “ሸገርን ማስዋብ” ፕሮጀክት ስንመረምር በዚህ ፕሮጀክት ስም በተሰበሰበው የሕዝብ ገንዘብ አዲስ አበባ መሀል የተቋረውና ሆራ ፊንፊኔ ብለው የሰየሙት ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለምን አላማ እንደታሰበ ግልጽ ይሆንልናል።
በመሰረቱ እሬቻ የኦሮሞ ገዢ መደብ በየስምንት አመቱ ሲያደርግ የኖረውን ወረራ ገና ሳያካሂድ፤ ኦሮሞ የእርሻ ስራና ሰብል ማምረት ሳይጀምርና ኦሮሞ ዛሬ ኦሮምያ የሚባለውን ምድር ሳይረግጥ መስከረም በገባና መስቀል በተከበረ በሳምንቱ ሲከበር የኖረ የአራሾች ክብረ በዓል ነው። እሬቻ በሸዋ ውስጥ በብዛት ይከበረ የነበረው ደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ሥፍራ በነበረው ዛሬ ሆራ ሐይቅ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ነበር።
እሬቻ የኦሮሞ በዓል አለመሆኑን በተጨማሪ ለማወቅ የቃሉን ፍቺ ማየትም ይቻላል። እሬቻ የሚለው ቃል የአማርኛ ቃል እንጂ የኦሮምኛ ቃል አይደለም። እሬቻ ኦሮምኛ ነው የሚል ቢኖር የቃሉን የኦሮምኛ ግንድና ቃሉ በኦሮምኛ እንዴት አንደሚረባ ማስረዳት ይጠበቅበታል።
የግዕዙ ሊቅ አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ “ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት” በሚል ባሰናዱት መዝገበ ቃላት ውስጥ ገጽ 1153 ላይ እንደጻፉት እሬቻ ዋናው ሰብል ደርቆ ከመታጨዱና በአውድማ ተወቅቶ ወደ ጎተራ ከመግባቱ በፊት ቀድሞ የደረሰው ተቆርጦ በበትር በመወቃት ወይም በእጅ ታሽቶ የሚቀመሰው እህል ይሉታል። ሌላው የግዕዝ ሊቅ ከሣቴ ብርሃን ተሰማም በ1951 ዓ.ም ባሳተሙት “የአማርኛ መዝገበ ቃላት” መጽሐፋቸው ገጽ 218 ላይ እረቻ ነባር የአማርኛ ቃል መሆኑን ይገልጹና ትርጉሙም መከር ከመድረሱ በፊት ቀደም ብሎ በመድረስ ለችግር ወይም ለመብል የሚውል ሰብል ይሉታል።
በመሆኑም የእሬቻ በዓልንም የሚያከበረው አራሹ ገበሬ ክረምቱን በሰላም እንዲያልፍ፤ ያዘመረው እህል ለፍሬ እንዲበቃና እሸት እንዲቀምስ ያስቻለውን ፈጣሪውን ለማክበር ነው። በመሆኑም የእሬቻ በዓል እህል የሚያበቅል አራሽ ገበሬ የሚያከብረው አመታዊ ዝክር ነው።
እዚህ ላይ የቦረና ኦሮሞው ወዳጄ ጎዳና ያዕቆብ እሬቻን የኦሮሞ ባሕል ለሚያደርጉት ኦነጋውያን የሰጠውን አስተያየት መጥቀስ አስፈላጊ ነው። ጎዳና እሬቻን አብረንህ እናክብር ለሚሉት ሰዎች የሰጠው አስተያየት እንዲህ የሚል ነበር፤
“እሬቻን አብረንህ ሳናከብር ላሉኝ ወዳጆቼ ከብቶቻቸውን ለማጠጣት የእግዜር ዝናብ ከሚፈልጉ ከዘላን ማኅበረሰብ የተገኘሁት ቦረና በሚን ሁሳብ ነው ዝናብ ቆመ ብዬ ምስጋና የሚያቀርበው? በሹፌርነት ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ሰው ነዳጅ ጠፋ ብሎ ምስጋና ሲያቀርብ ሰምታችኹ ታውቃላችኹ? አርብቶ አደሩ ቦረናስ አራሽ በበሬ ሆኖ ስለ ሰብል እና አዝመራው ተጨንቆ እንኳን ዝናብ ጠፋ አሁን ሰብሌን መሰብሰብ እችላለኹ የሚለው በምን መዋቅር ነው?”
ጎዳና እንዳለው ኑሮውን የከብት ጭራ እየተከተለ ውኃና ግጦሽ ፍለጋ የሚንከራረት ዘላን የማይመለከተውን በእርሻ የሚተዳደሩ አርሷደሮችን በዓል ያከብራል ካልተባለ በስተቀር የከብት ጭራ እየተከተለና ውኃና ግጦሽ ፍለጋ የሚንከራተት ዘላን ዝናብ ቆመ ብሎ ምስጋና ማቅረብ በሹፌርነት ልጆቹን የሚያስተዳድር የቤት ባለቤት ነዳጅ ጠፋ ብሎ ለፈጣሪው ምንጋና እንደማቅረብ አይነት ጤና የጎደለው ተግባር ነው።
የኦሮሞ ብሔርተኞቹ እነ ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ዶክተር ነገሶ ጊዳዳ፤ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ አቶ ይልማ ደረሳ፤ ፕሮፈሰር ተሰማ ታዓ፤ ወዘተ እንደነገሩን ደግሞ ኦሮሞ ከብት በማርባት የሚተዳደር የነበረ ሲሆን የእርሻ ስራ የጀመረው ደግሞ ዛሬ በሰፈረበት አካባቢ ካገኛቸው የኢትዮጵያ ነገዶች ተምሮ መሆኑን ነግረውናል። ዘመኑም ከ17ኛውና ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ነው። ይህ ማለት የተሰማራበት የስራ መስክ ከብት ማርባት፤ እምነቱ ደግሞ ዋቄ ፈና ነው የተባለው ኦሮሞ የማያበቅለው እህል የሚሽትበትን ወቅት ጠብቆ ሃይማኖቱ አይደለም የተባለውን መስቀልን አሳልፎ መስቀል በሆነ በሳምንቱ እህል እንዲያበቅል፤ እሸት እንዲቀምስ ለሚያስችል ፈጣሪ ምስጋና ሊያቀርብ ይችላል ካልተባለ በስቀር ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ እሬቻን ማክበር የጀመረው ሸዋን ሲወር ያገኛቸው አራሽና እህል አብቃይ የአማራ ገበሬዎች ያመረቱት ሰብል ለፍሬ እንዲበቃና እሬቻ [እሼት] እንዲቀምሱ ላስቻላቸው ፈጣሪያቸው ያቀርቡት የነበረውን የምስጋና ባሕል በመውረስ ነው።
ስለዚህ እሬቻ ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ ከነ ቃሉ ከሰብል አምራች የአማራ አርሶ አደሮች የወረሰው የምስጋና በዓል፣ ቃሉም አማርኛ ሲሆን ኦሮሞ አካባቢውን ከመውረሩ በፊት ጀምሮ ይከበር የነበረው ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ እየተባለ በሚጠራው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ እንጂ አዲስ አበባ ውስጥ አልነበረም።
ይህ እውነት ቢሆንም ቅሉ የኦነጋውያን ኦሮሙማ ማዕከሉ ዘረፋ፣ ወረራና ቅሚያ ስለሆነ አዲስ አበባን ዳግማዊ ምኒልክ የጥንቱን በራራ ፍራሽ አድሰው እንደገና ከማቆማቸው በፊት የነበሩት ኦሮሞዎች፤ እሬቻም ከነ ቃሉ የኦሮሞ አይደለም፤ አዲስ አበባ ውስጥም ተከብሮ አያውቅም የሚለው የታሪክ እውነት ደንታ አይሰጣቸውም። ኦነጋውያን እንኳን በአዲስ አበባ ዙሪያና በመላው አገሪቱ የሚገኘው ኦሮምኛ ተናጋሪ ቀርቶ ከቦረና ውጭ ያለው ኦሮምኛ ተናጋሪ በወራሪ አባገዳዎች መሬቱን የተቀማ፣ ማንነቱን በኃይል የቀየረና ኦሮምኛ ቋንቋ በግዳጅ እንዲናገር የተደረገ እንጂ ኦሮሞ አለመሆኑን ኦሮሞዎ ብሔርተኞቹ እነ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕሮፈሰር መሕመድ ሐሰን፣ ወዘተ እንኳ ያጠኑትን ታሪክ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ ሕመምተኞች ናቸው። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ትክክለኛ ኦሮሞዎቹ ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። ከነሱ ውጭ ያለው ነባሩ ሕዝብ ተገዶ ኦሮምኛ እንዲናገር ተደረገ እንጂ ኦሮምኛ ስለተናገረ ኦሮሞ አይደለም።
ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮምኛ እንዳልሆነ እውነተኞቹ ኦሮሞዎቹ ራሳቸው ምስክር ናቸው። በእውነተኞቹ ኦሮሞዎች ትውፊት ውስጥ «Saglan Borana, sagaltamman garba» የሚል አባባል አለ። ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ዘጠኙ ኦሮሞ ነው፤ ዘጠናው ገርበ ነው» ማለት ነው። ገርበ ኦሮሞ ሲስፋፋ ያስገበራቸውንና ባርያ ያደረጋቸውን ነገዶች የሚጠራበት ስያሜ ነው። በኦሮሞ በራሱ ትውፊት መሰረት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከሚኖረው ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝበ መካከል ትክክለኛው ኦሮሞ ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከአስሩ ዘጠኙ ገርበ ወይም በአባገዳዎች በወረራ የተያዘና በኃይል ኦሮሞ የተደረገ ሕዝብ ነው።
ይህንን እውነት ከኦሮሞዎች ትውፊት በተጨማሪ ዛሬ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። የሰላሌና አምቦ ሕዝብ የDNA ውጤት እንደሚያሳየው ዝምድናው ከምንጃርና ወይም ጅሩ ሕዝብ ጋር እንጂ ከቦረና (እወነተኛው ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ፖል ሶሊሌት የተባለው የፈረንሳይ ጎብኝ እ.ኤ.አ. በ1884 ዓ.ም. ሸዋን ጎብኝቶ በጻፈው የጉዞ ማስታወሻው በሰላሌና ጃርሶ ውስጥ ኦሮሞ ገርበ ያደረጋቸው የአካባቢው ቀደምት ባለይዞታዎች አማሮች እንደሆኑ ጽፏል።
የአርሲ ሕዝብ ዝምድናው ከሐዲያ ጋር እንጂ ከቦረና ጋር አይደለም። ጀርመናዊው የታሪክ ምሁር በርካምበር እንዳጠናው ከአርሲ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሐድያ ነው። የጅማ ሕዝብ ከየምና ከከፋ ሕዝብ እንጂ ከኦሮሞ ጋር ምንም ዝምድና የለውም። አባጅፋር ራሱ አረብ እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ወለጋ እውነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስርም አይሞሉም። እውነተኛ ኦሮሞዎቹ ለባሪያ ፍንገላና ውሀና ሳር ፍለጋ መጥተው ሌላውን ገርበ አድርገው የቀሩት አባገዳዎችና ልጆቻቸው ብቻ ናቸው።
የትኛውም ብሔርተኛ ቢሆን አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር አይቻለውም። በየትኛውም አለም ብሔርተኛ ሆኖ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር ሲያፈርስን እንጂ አገር ሲያረጋጋና ሲያስተዳድር ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ታሪክ በብሔርተኛነት እሳቤ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር የማስተዳደር እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ ያለው አገዛዝ የለም። የኦሮሞ ብሔረተኞም ዓላማቸው ወንድምን በወንድም ላይ እኅትን በእኅት ላይ በማስነሳት የኦርሞ ኤምፓየር ቅዠታቸውን ማሳካት እንጂ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር የማስተዳደር ፍላጎት፣ እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ የላቸውም።
ከነገዳቸው ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላውን ዘረፋን፣ ወረራንና መውረስን ፖለቲካቸው ያደረጉ ያበዱ ብሔርተኞች መንግሥት ይሆኑናል ብሎ ማሰብ ውሻ ነከሰኝ ብሎ ለጅብ አቤት እንደማለት አይነት የዋህነት ነው። ብሔርተኛ ሁሉ አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር እንደማይችል ያለፉት አርባ አራት አመታት የኢትዮጵያ የቁልቁለት መንገድ ምስክር ነው። ልክ በቅሎ እንደማትወልድ ሁሉ የነገዱ ሳይሆን የኢትዮጵያ ስነ መንግሥት እሳቤ የሌለው፣ ከነገዱ ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት ያልያዘ ማናቸውም አይነት የሁሉም መንግሥት የመሆን ችሎታ የለውም። ያለው ችሎታ ቢኖር እንደ ወያኔና ኦነግ የሌላውን መዝረፍ፣ መቀማት፣ መቀራመት፣ መውረስና የተሰራ አገር ማፍረስ ብቻ ነው።
ባጭሩ እሬቻ በኦሮሞ ብሔርተኞች የተዘረፈ እንጂ ኦሮምኛም የኦሮሞም አይደለም። እሬቻ ኦሮሞ ከባንቱ ወርሶ ኢትዮጵያን ከወረረበት የገዳ ሥርዓት ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም። እሬቻ የኦሮሞ በዓል/ባሕል ቢሆን ኖሮ የሚከበረው አንጋፋው ኦሮሞ በሰፈረበት በከብት አርቢው ቦረና እንጂ ከቦረና 600 ኪሎ ሜትሮች በላይ ርቆ በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ ገበሬዎች በሚኖሩበት ደብረ ዘይት አይደለም።
እሬቻ የሚባልም የአማርኛ እንጂ የኦሮምኛ ቃል የለም። እሬቻ የሚል ስር ያለው የኦሮምኛ ቃል የለም። ባለፈው ዓመት እሬቻ ቃሉም ሆነ ባሕሉ የኦሮሞ አለመሆኑን በጻፍሑት ጽሑፍ ላይ አንዱ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፕሮፈሰር ባቀረበው ትችት እሬቻ አሮምኛ ነው፤ “ህርሱ” የሚል ቃል በኦሮምኛ ውስጥ አለ፤ ትርጉሙም መስጠት ማለት ነው፤ ስለዚህ እሬቻ የተወሰደው ከህርሱ ነው የሚል መልስ ቢጤ ጽፎ ነበር። ይህ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፕሮፈሰር ግን የበዓሉ ትርጉም ህርሱ የሚል የኦሮምኛ ቃል ከሆነ በዓሉ ኦሮምኛ ወዳልሆነው ወደ እሬቻ ለምን እንደተቀየረ አልነገረንም። በዓሉ የኦሮሞ ከሆነ፣ ቃሉም ኦሮምኛ ከሆነ በዓሉ ህርሱ ተብሎ ለምን እንደማይከበር፤ በእርሻ የሚተዳደሩ ገበሬዎች የሚያከብሩትን ይህን በዓል ቀዳሚው ኦሮሞና ከብት አርቢው ቦረና ሳያከብረው ገርባው ብቻ ለምን እንደሚያከብረው መልስ የሰጠ ሰው እስካሁን አላየንም።
በእውነቱ እሬቻ የኦሮሞ ባሕል ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ፤ በዓሉንም ከሁሉ በፊት እሬቻን ሊያከብሩት የሚገባቸው ገርባዎች ሳይሆኑ ትክክለኞቹ ኦሮሞዎች ቦረናዎች ነበር። ያልተበረዘው ቀዳሚው ኦሮሞ የሆነው ቦረና የማያከብረው በዓል የኦሮሞ በዓል አይደለም። ቦረና ራሱ እሬቻን የገርባ በዓል ነው የሚለው።
እሬቻ የኦሮሞ ባሕል አለመሆኑን ለማወቅ ቃሉ አማርኛ እንጂ ኦሮምኛ አለመሆኑን፤ በዓሉም በእርሻ የሚተዳደሩ እንጂ የከብት አርቢዎች በዓል አለመሆኑን፤ በዓሉ ኦሮሞ የእርሻ ስራን ከመልመዱ ዘመና በፊት ዛሬ በሚከበርበት በደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ በአማሮች ሲከበር የኖረ በዓል መሆኑን፤ ገርባው እንጂ ያልተበረዘውና ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ቃሉንም ሆነ በዓሉን የማያውቀው መሆኑን፤ ይልቁንም እሬቻ ሲከበር የኖረው ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ከሚኖርበት 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ መሆኑን ማስታወስ በቂ ነው።
ቦረና የማያከብረውን በዓል ገርባው የኦሮሞ ነው ብሎ ማክበሩ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ገርባው ኦሮሞ አለመሆኑን ብቻ ነው። እሬቻ የኦሮሞ ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ ይሆን ነበር፤ በዓሉም በገርባው ምድር ሳይሆን ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነ ቦረና በሚኖርበት በቦረና ምድር እንጂ ቦረና ከሚኖርበት አካባቢ 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ ገርባ እንጂ ቦረና በማይኖርበት ምድር በሸዋ ውስጥ አይከበርም ነበር። ይኼው ነው።
የአበበ ገላው ነገር
ክፍል ፩
አበበ ገላው በትናንትናው እለት በከፈተው የዩቱብ ሱቅ በኩል ባሰራጨው ቃለ መጠይቁ ዐቢይ አሕመድ እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. ግንቦት ወር “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” እንዳለው እና ይህ የዐቢይ አባባልም እንደ ኤሌክትሪክ እንደነዘረው፣ ዐቢይ አሕመድን በጥርጣሬ ዐይን እንዲያየው እንዳደረገውና ውስጡ እንደነቀለቀው ነግሮናል። ምንም እንኳን ዐቢይ አሕመድ በሚሊዮን አመታት ውስጥ አማራ ኢትዮጵያን እንዳይመራ የነገረውና ውስጤ ቀረ ያለውን ጉዳይ በደንብ እንዲገባው በአማርኛ ብቻ ሳይኾን አጽንኦት ለመስጠት የእንግሊዝኛ አገላልጽ ጭምር በመጠቀም ቢነግረውም ቅሉ አበበ ገላው ግን ነገሩ የአፍ ወለምታ ስለመሰለው ወደ አደባባይ ሳያወጣው እስካኹን ድረስ ጸጥ ብሎ እንደቆየ ሊያስረዳን ሞክሯል። ይገርማል!
አበበ ገላው በትናንትና እለት “የቤተ መንግስቱ ሚስጢር!” የሚል ርዕስ የሰጠውን ሸቀጥ እንካችኹ ሊለን የሚቃጣው ዐቢይ አሕመድን እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. በግንቦት ወር አግኝቶት “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ካለው በኋላ ዐቢይ አሕመድን በጥርጣሬ ዐይን ተመልክቶት ስለሱ ሳይተነፍስ ከርሞ ትናንትና መናገር የጀመረ እንጂ ዐቢይ አሕመድን ሲያመልክ የከረመ፤ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ሲል ኦዴፓ ያወጣውን መግለጫ ዐቢይ አሕመድን የሚነካበት ስለመሰለው መግለጫው የኦሮምያ ክልል ተብዮው እንጂ የፓርቲው የኦዴፓ አይደለም እያለ ሲጃጃል የከረመው፤ የውሸት የትምህርት ማስረጃው የእውነት እንደኾነ ሽንጡን ገብሮ ከእኔ ጋር ሲከራከር የነበረ አይመስል። ልብ በሉ! አበበ ይህንን ሁሉ ያደረገው ዐቢይ አሕመድን አግኝቶ “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ካለው በኋላ ነው።
እኔ እንደማስበው አበበ ገላው በደጅ ጥናት ተሳክቶለት ዐቢይ አሕመድን ካገኘው በኋላ የእንግሊዝኛ አጽንኦት ጨምሮ “ከእንግዲህ አማራ ኢትዮጵያን አይመራም” ካለው በኋላ ምንም ሳይመስለው ስለ ዐቢይ አሕመድ ልዕለ ሰብዕ መሆንና በውሸት ያከማቸውን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛ ስለመሆኑ ለማስረዳት ሲጋጋጥ የነበረው ትናንትና ሊነግረን እንደሞከረው “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ሲል ዐቢይ በቤተ መንግሥት የነገረው ገር የአፍ ወለምታ ስለመሰለው “አፉ” ብሎት ሳይኾን በሀሳቡ ስለሚስማማ ነው።
የአበበ ገላው እናት ድርጅት የኾነው ግንቦት ሰባት የኦባማን መመረጥ ተከትሎ በርዕሰ አንቀጹ ቁጥር 27/2001 ዓ.ም. ላይ እንዳወጀው ድርጅቱ የሚታገለው የፖለቲካ ስልጣንን ለአስርተ መቶዎች አመታት እየተፈራረቀ ሲገዛ ከነበኖረው ከአማራና ከትግሬ ወደ ኦሮሞውና ደቡቡ ለማሸጋገር እንደኾነ አውጇል። ስለዚህ የአበበ ገላው ጠቅላይ ሚኒስትር የተሰየመው ከኦሮሞ ስለኾነና አበበና ድርጅቱም የታገሉት ከእንግዲህ በኋላ አማራ ኢትዮጵያን እንዳይገዛ ስለኾነ እሱና ድርጅቱ የታገሉለት አላማ ስለኾነ አማራ በሚሊዮን አመታት ውስጥ ኢትዮጵያን እንደማምመራ ሲነገረው የትግሉ ፍሬ ስለኾነ የሚስማማበት እንጂ ዛሬ ለዩቱብ ሸቀል ሲል ሊነግረን እንደሚሞክረው ውስጡን የነቀነቀው የአፍ ወለምታ አልነበረም።
አበበ ገላው የአፍ ወለምታና አስተሳሰብ የተለያዩ መኾናቸው የሚያውቅ አይመስልም። የአፍ ወለምታ በንግግር በሀል በድንገት አንዳልጦ የሚገባ አንድ ቃል እንጂ በአንድ ሙሉ የአማርኛ አረፍተ ነገር የተነገረና የእንግሊዝኛ አጽእኖት የታከለበት አስተሳሰብ አይደለም። በሌላ አነጋገር “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም” የሚለው አረፍተ ነገር እና “Not in a million years!” የሚል አጽእኖት የተጨመረበቱ አገላለጽ መሰረታዊ አስተሳሰብ እንጂ የአፍ ወለምታ አይደለም። ዐቢይ አሕመድ “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ሲል ለአበበ ገላው የገለጽለትም መሰረታዊ አስተሳሰቡን እንጂ አፉ አንዳልጦት የሳተው የአፍ ወለምታ እንዳልኾነ አበበ ገላውም ያውቀዋል።
አበበ ገላው ይህንን የዐቢይ አሕመድ መሰረታዊ አስተሳሰብ ከፈረሱ አፍ ከሰማ በኋላ አምልኮተ ዐቢይ አሕመድ ውስጥ ገብቶ የውሸት የትምህርት ማስረጃውን ሳይቀር ለመከላከል ሲራኮት የከረመው የዐቢይ የትምህርት ማስረጃ የውሸት መኾኑ ሲጋለጥ አበበ ገላውና ድርጅቱ ግንቦት ሰባት የታገሉለት የፖለቲካ ስልጣንን ከአማራና ከትግሬ ወደ ኦሮሞውና ደቡቡ የማሸጋገር አላማቸው እንዳይደናቀፍ በማሰብ ነው።
አረመኔው ዐቢይ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የዘር ፍጅት፣ ማፈናቀል፣ ዘረፋና አማራ አያሳየኝ ብሎ ወደ ማሰቃያና ማጎሪያ ቄራ ማጋዝ የጀመረው ዛሬ አበበ ገላው መናገር ሲጀምር አይደለም። አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ በመደበለት ሪፑብሊካን ጋርድ እየተጠበቀ [ምንም እንኳን አበበ ይህንን ከዐቢይ አሕመድ እንዳገኘው ጥቅም ባይቆጥረውም] ከዲሲ- አዲስ አበባ ሲንሸራሸርባቸው በከረመባቸው ያለፉት አመታት ሙሉ የአማራ ሕዝብ አማራ አያሳየኝ ባለው ዐቢይ አሕመድ የጅምላ ፍጅት፣ የዘር ማጥፋትና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ሲካሄድበት ነው የኖረው።
በነዚህ ዓመታት ውስጥ አበበ ገላውና መሰሎቹ አረመኔው ዐቢይ አሕመድ አማራ አያሳየኝ ብሎ በአማራ ሕዝብ ላይ ሲያካሂደው የከረመውን የጅምላ ፍጅት፣ የዘር ማጥፋትና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በመቃወማችን በጽንፈኛነት ሲከሱን ነበር። ይህንን አበበ ራሱ ለዐቢይ አሕመድ ጻፍኹት ባለው ኢሚል ላይም አንስቶታል። ዐቢይ አሕመድ አማራ አያሳየኝ ብሎ አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያቋቋመውን የስናፍጭ ቅንጣት ያህል የመንግሥትነት ጠባይ የሌለው የኦሮሙማ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የዘር ማጥፋት፣ የቅሚያ፣ የሥርቆትና የወንጀል ድርጅት የሚቃወሙ የአማራ ተወላጆችን አበበ ገላው እንደ ጽንፈኛ ነው የሚያያቸው።
ባጭሩ አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. ግንቦት ወር “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ሲል ነገረኝ ካለበት አመት ወዲህ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ አረመኔው ዐቢይ አሕመድ አማራ አያሳየኝ ብሎ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት፣ ዘረፋ፣ ገፈፋና የጅምላ እልቂት ሲካሄድበት በኖረባቸው አመታት ውስጥ ዝም ብሎ ከርሞ ዛሬ የአማራ ሕዝብ እውነተኛ የኅልውና ተጋድሎ ሲጀምር ዐቢይ አሕመድ ከአራት አመታት በፊት “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ብሎኝ ነበር በማለት “የቤተ መንግስቱ ሚስጢር!” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ዛሬ እንደነገረው አድርጎ ሸቀጡን ይዞ በዩቱብ ብቅ ያለው የሚያንጠለጥለው አዲስ ማተብ ፍለጋ እንጂ አማራ በሚሊዮን ዓመታት ውስጥ ስልጣን እንደማይዝ ለአበበ ገላው በነገረው ወቅት ያልነበረውን አዲስ አመል ዛሬ ስላመጣ አይደለም።
አበበም ለዩቱቡ ሱቅ ማድመቂያ ዛሬ ፈልፍሎ እንደደረሰበት አዲስ ግኝት ኹሉ ከአራት አመታት በፊት ነገረኝ ያለውን አምስት አመታት ሙሉ በተግባር ሲለውጥ የባጀውን አረመኔነት ዛሬ “የቤተ መንግስቱ ሚስጢር!” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ይዞት ብቅ ማለቱ ለዩቱብ ሽቀላ እንጂ ባለፉት የዐቢይ አሕመድ አምስት የጭካኔ አመታት ውስጥ አማራን በሚመለከት በመሰረተ ሀሳብ ደረጃ ከዐቢይ የተለየ አስተሳሰብ ስለነበረው አይደለም። በእውነቱ አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ ነገረኝ ካለው የተለየ አስተሳሰብ ቢኖረው ኖሮ ጋዜጠኛነት ተምሬያለኹ እያለ ከአራት አመት በላይ የኾነውን ቀንድ ነገር ይዞ እንደ ሰበር ዜና “የቤተ መንግስቱ ሚስጢር!” የሚል ርዕስ ሰጥቶ እንደ ትኩስ ጉዳይ እንካችኹ ሊለን ከአራት ዓመታት በኋላ ባልመጣ ነበር።
የኾነ ኾኖ አበበ ገላው ዛሬ ላይ ደረስኹበት የሚለው አቋም የብልጣብልጥነትና ለዩቱብ ሽቀላይ ተብሎ ሳይኾን ወደ ውስጡ አይቶ የደረሰበት ሚዛን ቢሆን ኖሮ ከሁሉ በፊት አዲስ አበባን የኦሮሞ ናት ያለው ዐቢይ አሕመድ የሚመራው ኦዴፓ ሳይኾን የኦሮምያ ተብዮው ክልል ነው፤ በዐቢይ አሕመድ ላይ እኔ ጥያቄ የለኝም፤ ሌሎችም ሊኖራቸው አይገባም፤ ዐቢይን የመሰለ ብቃት ያለው መሪ ኢትዮጵያ ኖሯት አያውቅም፤ ዐቢይ አሕመድ በወያኔ ዘመን ስልክ መጥለፍ የለብንም ብሎ ስለ እኛ ከነ መለስ ጋር ተጣልቶ ከኢንሳ ተባሮልናል፤ የአንድ ክፍለ ከተማ ሕዝብ አፈናቅሎ በ49 ቢሊዮን ብር በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት ቅንጡ ቤተ መንግሥት እየገነባ ያለን አረመኔ ቤተ መንግሥት ሳይኾን ትናንት ቢሮዎች ነው የሚያስፈልጉን ብሎ የሚያስብ የሕዝብ መሪ፣ የሕዝብ ጉዳት የሚጋራ መሪ ወዘተ… እያለና የዐቢይ አሕመድን የውሸት የትምህርት ማስረጃ ለመሸፈን “የሚስጥሩ ቁልፍ” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ዶክተምተሪ በማዘጋጀት ያሳሳተቸውን ሰዎች ይቅርታ ጠይቆ ራሱን ለሕዝብ ፍርድ ማቅረብ ነበረበት።
ይህ ትር እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. ኀምሌ ወር የዐቢይ አሕመድ የትምህርትና ወታደራዊ ማስረጃ የውሸት እንደሆነ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የጻፍኹት ጥናታዊ ጽሑፍ ነው።
ይህ ጽሑፍ በድጋሜ እ.ኤ.አ. በ2020 ዓ.ም. በድጋሜ ታትሟል፤ ይህንን ትር በመጫን መመልከት ይቻላል።
ይህን ተከትሎ ሌሎች ሰዎች ጭምር የዐቢይን የትምህርት ማስረጃ ውሸትነት ስላስተጋቡት ይህንን በመቃወም አበበ ገላው ዶክመንተሪ ፊልም አዘጋጅቶ ተከሰተ። ማስረጃ አሰባስቤ አጠናሁት ባለው የዐቢይ አሕመድ የትምህርት ማስረጃ የዐቢይ አሕመድ የትምህርት ዝግጅትና ዲግሪዎቹ ውሸት እንደሌለት በከፍተኛ አድናቆት የታጀበ ውዳሴ ዐቢይ ይዞ ብቅ አለ። ይህንን አበበ ገላው ጠለቅ ብየ አጠናኹት ያለውን ዶክመንተሪ ይህንን ትር በመጫን መመልከት ይቻላል፤
https://www.facebook.com/…/pfbid021GXX2yndbCWprXYBMP8EM…
አበበ ገላው “የሚስጥሩ ቁልፍ” ሲል ያዘጋጀውን ዶክመንተሪ ተከትሎ እኔ የሰጠኳቸው መልሶችና አበበ ገላው የሰጣቸው ግብረ መልሶችን የሚከተሉትን ትሮች በመጫን ማንበብ ይቻላል፤